ለምንወደው የምንሰጠው የፍቅር ስጦታ

Publication15.jpgለምንወደው ሰው ምን አይነት የፍቅር ስጦታ ልስጠው ብላችሁ ብታስቡና እና የመረጃ መረብን ብትጠይቁ የፍቅር ስጦታ ሃሳቦች የሚል ብዙ አማራጭ ታገኛላችሁ፡፡ ለምትወደው ሰው እንደዚህ አይነት ስጦታ ብትሰጠው መልካም ነው የሚል ሃሳብ ይሰጣችኋል፡፡ ለዚህ በአል ይህንን ስጦታ ብትሰጠው ሰው ደስ ይለዋል የሚል ብዙ የስጦታ ሃሳቦችን ታገኛላችሁ፡፡ ለምትወዱት ሰው ስጦታ መስጠት ፈልጋችሁ ምን መስጠት እንዳለባችሁ ለየት ያለ የፈጠራ ሃሳብ እንዲሰጣችሁ የመረጃ መረቡን ትጠይቁ ይሆናል፡፡ ይህንን አይነት ቀለም ያለው አበባ ለዚህ አጋጣሚ ብትሰጥ አጋጣሚውን ልዩ ያደርገዋል በማለት የተለያየ ሃሳቦችን ይሰጣችኋል፡፡ አጠያይቃችሁ ሰዎች አማክራችሁ እንኳን ስጦታችሁ ላይሰምር ፣ ተቀባይነት ላያገኝ ፣ ላይወደድ ብሎም ላይጠቅም ይችላል፡፡

እኔ ደግሞ ሰው ለሚወደው ሰው ምን አይነደግሞ ሰውስጦታ ሊሰጥ እንደሚችል መፅሃፍ ቅዱስን አገላብጫለሁ፡፡ ሰው ለሚወደው ሰው የሚሰጠው ልዩ የሆነን የስጦታ ሃሳብ ስላገኘሁ ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡ ይህ ስጦታ እንደ አበባ ስጦታ ፣ እንደ ልብስ ፣ እንደ ጌጣጌጥ ስጦታ በገንዘብ የሚገመት ስጦታ አይደለም፡፡ ይህ ስጦታ የሚቀበሉትን ሁሉ የሚባርክ እንደ እግዚአብሄር ቃል የሆነ ስጦታ ነው፡፡

ይህ ስጦታ የሰዎች ህይወት የሚለውጥ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስጦታ ሰዎችን የሚያበረታ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስጦታ ሰዎችን የሚያነሳ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስጦታ የሰዎችን ህይወት የሚለውጥ ስጦታ ነው፡፡ ይህ ስጦታ እራሳችንን ለፀሎት የምንሰጥበት የምልጃ ፀሎት ነው፡፡

ምልጃ በሌላ ሰው ቦታ ለሌላ ሰው በእግዚአብሄር ፊት የምንጠይቅበት ፀሎት ነው፡፡ ይህ የምልጃ ፀሎት የሌላውን መስማማት ወይም አለማስማመት አይጠይቅም፡፡ የሚማልድለት ሰው እንደሚማልድለት እንኳን ላያውቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን የምልጃው ውጤት ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ይህ ፀሎት በሌላው ሰው ቦታ ሆነን ፣ የሌላው ሰው ስሜት እየተሰማን ፣ የሌላው ሰው ህመምን እየታመምንና የሌላውን ሸክም እንዳራሳችን ሸክም እየተሸከምን የምንፀልየው የፀሎት አይነት ነው፡፡

ምልጃ ሌላው ሰው መፀለይ በማይችልበት ጊዜ በእርሱ ፋንታ ሆኖ የሚፀለይ ፀሎት ነው፡፡ ምልጃ ሌላው ሰው በማይረዳበት ሁኔታ የእግዚአብሄርን ሃሳብ ተረድቶ ስለሌላው ሰው የሚደረግ ልመና ነው፡፡

ጴጥሮስ የሚያደርገውን በማያውቅበት ጊዜ ይህንን የተመለከተው ኢየሱስ ስለ ጴጥሮስ ማለደ፡፡

ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ። ሉቃስ 22፡32

ለቅዱሳን መዳን ማሸነፍና መውጣት ልንማልድ ይገባናል፡፡

በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤ ኤፌሶን 6፡18

ስለሚወዱን ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለሚጠሉንም ሰዎች ልንሰጣቸው የምንችለው ድንቅ ስጦታ ስለ እነርሱ በእግዚአብሄር ፊት መማለድ ነው፡፡ ስለሰዎች በእግዚአብሄር ፊት መቅረብ ልዩ ስጦታ ነው፡፡

ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ ማቴዎስ 5፡44

ኢየሱስም፦ አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። ልብሱንም ተካፍለው ዕጣ ተጣጣሉበት። ሉቃስ 23፡34

ጌታን ሰለሚያውቁትም ስለማያውቁትም መማለድ ለሰዎች የምንሰጣው ልዩ ስጦታ ነው፡፡

. . . ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡1-2

ይህንን ምልጃ የምናደርገው በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና እርዳታ ነው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እብሮ ለመቃተት ግን ራሳችንን ማዘጋጀትና ጊዜን መስጠት የሚጠበቀው ከእኛ ነው ፡፡

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ሮሜ 8፡26

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #ፀሎት #እግዚአብሄርንመፈለግ #ማማጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #አላማ #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መቃተት #መንበርከክ #መጠበቅ #ትግስት #መሪ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on December 12, 2017, in Prayer. Bookmark the permalink. Comments Off on ለምንወደው የምንሰጠው የፍቅር ስጦታ.

Comments are closed.

%d bloggers like this: