ጤናማ ያልሆነ ምግብ – ጤናማ ያልሆነ ህይወት

injera.jpgምግብ ለሰው ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ነው፡፡ ምግብ ለሰውነት ጠቃሚ ቢሆንም በንፅህና ካልተያዘና ጤንነቱ ካልተጠነቀ የሚጠቅመውን ያህል ሊጎዳ ይችላል፡፡ ምግብ ለሰው እድገትና ውጤታማነት ወሳኝ አንደ መሆኑ መጠን የምንመገበውን ምግብ ንፅህናና ጤንነት ካለተረጋገጠ በዛኑ መጠን አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡

መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4፡1-2

እንምዲሁም ለመንፈሳዊ እድገት መንፈሳዊ ምግብ ወሳኝ ነው፡፡ የምንመገበውን ምግብ ንፅህናና ጤንነት መከታተል ከመንፈሳዊ ድካምና በሽታ እንድንጠበቅ ያስችለናል፡፡

በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር። ነገር ግን በሰው ሁሉ ፍርሀት ሆነ፤ በሐዋርያትም እጅ ብዙ ድንቅና ምልክት ተደረገ። ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤ ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር። በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ፥ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር። ሐዋሪያት 2፡42-47

በተፈጥሮአዊ ታንታመም የህመማችን መንስኤ የምግብ መበከል መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እንዳሉ ሁሉ ከበላነው ጤናማ ያልሆነ ሚዛኑን ያልጠበቀ እንደእግዚአብሄር ቃል ያልሆነ ምግብ የተነሳ መንፈሳዊ ጤንነታችን ሲታወክ የሚያሳየው ምልክት አለ፡፡

እንዲሁም ጤናማ መንፈሳዊ ምግብ የተመገበ ሰው የሚያሳየው ህይወት ያለ ሲሆን ጤናማ ያልሆነ ምግብን የተመገበ ሰው እንዲሁ የሚታወቅበት ባህሪዎች አሉ፡፡

ጤናማ ያልሆነ መግብ ምልክቶች

  1. ጤናማ ያልሆነ ምግብ የተመገበ ሰው ሌላ ምግብ ያስጠላዋል

ንፁህ ምግብ ጤናማ ያደርጋል፡፡ ጤናማ ምግብ ለሌላ ምግብ ፍላጎት ይከፍታል፡፡ ጤናማ ምግብ የሰውን የምግብ ፍላጎት አያውክም፡፡ ጤናማ ያልሆነ ምግብ ግን የተመገበው ሰው ለሌላ ምግብ ፋላጎት እንዲያጣ ያደርገዋል፡፡ የተሳሳተ ምግብ የበላ ሰው ለእግዚአብሄር ቃል ትምህርት ፍላጎት ያጣል፡፡

ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና። ማቴዎስ 5፡6

  1. ጤናማ ያልሆነ ምግብ የተመገበ ሰው ፍላጎቱ ይበላሻል፡፡

የተበላሸ ምግብ የበላ ሰው ፍላጎቱ ከጤነኛ ሰው ፍላጎት የተለየ ይሆናል፡፡ ንፁህ ምግብ የበላ ሰው ፍላጎቱ መውጣት መግባት መስራት ሲሆን የተበላሸ ምግብ የበላ ሰው ግን ፍላጎቱ ከዚህ ይለያል፡፡ ጤናማ ምግብ የበላ ሰው እግዚአብሄርን ማመስገን ፣ ክርስቶስን መከተል ለእግዚአብሄር መኖር የዘወትር ፍላጎቱ ነው፡፡ የተሳሳተ ምግብ የበላ ሰው ግን ምስጋና ከህይወቱ ይጠፋል፡፡ የተሳሳተ ምግብ የበላ ሰው እንደጎደለው ድሃ እንደሆነ እንዳጣ ይሰማዋል፡፡ የተሳሳተ ምግብ የበላ ሰው ሃብታም አንዳልሆነ የሚጎድለው እንዳለ ምስኪን እንደሆነ ይሰማዋል፡፡ ጤናማ ምግብ ያልበላ ሰው በምስጋና ልብ እግዚአብሄርን ማገልገል ያቅተዋል፡፡ ጤናማ ምግብ ያልበላ ሰው ለእኔስ ማን አለኝ በማለት በራስ ወዳድነት ላይ ያተኩራል፡፡ ጤናማ ምግብ ያልበላ ሰው ሌሎችን መድረስ ለሌሎች በረከት መሆን ሌሎችን መጥቀም ሞኝነት ይመስለዋል፡፡

መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። ፊልጵስዩስ 3፡19

የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ዕብራዊያን 12፡15-16

  1. ጤናማ ያልሆነ ምግብ የተመገበ ሰው ኢየሱስን አተኩሮ ማየት ይቸግረዋል፡፡

ጤናማ ምግብ ያልተመገበ ሰው ትኩረቱ ኢየሱስ ላይ ሳይሆን ሌሎች ነገሮች ላይ ይሆናል፡፡ ጤናማ ምግብ ያልተመገበ ሰው ሃሳቡ ምድራዊ ይሆናል፡፡ ጤናማ ምግብን ያልተመገበ ሰው እይታው የቅርብ ብቻ ይሆናል፡፡ ጤናማ ምግብን ያልተመገበ ሰው ስለዘላለማዊ ህይወት ማሰብ አቅም ያጣል፡፡

እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2

እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብራውያን 12፡1-2

  1. ጤናማ ያልሆነ ምግብ የተመገበ ሰው ትህትና አይኖረውም፡፡

ጤናማ ምግብ የተመገበ ሰው ምልክቱ ትሁት ይሆናል፡፡ እግዚአብሄርን መረዳት ምልክቱ ሰው በእግዚአብሄር ፊት ያሱን ያዋርዳል፡፡ ጤናማ ምግብ ያልተመገበ ሰው ትህትና የለውም፡፡ ጤናማ ምግብ ያልተመገበ ሰው ሰዎችን ይንቃል፡፡ ጤናማ ምግብ ያልተመገበ ሰው ለአንድነት ግድ የለውም፡፡ ጤናማ ምግብ ያልተመገበ ሰው ለሌሎች እውቅና አገልግሎት መስጠት አይፈልግም፡፡ ጤናማ ምግብ ያልተመገበና መንፈሳዊ ጤንነቱ የተዛባ ሰው በትህትና ከሌላው ጋር መስራት አይፈቅድም፡፡ ጤናማ ምግብ ያልተመገበ ሰው የራሱን ብቻ ነው የሚፈልገው፡፡

አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል። እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡26-27

እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5፡5-6

  1. ጤናማ ምግብ ያልተመገበ ሰው ለእግዚአብሄር ለመስጠትና ለመሰጠት አቅም ያጣል

በተፈጥሮ ምግብ ለስራ ጉልበት እንደሚሰጥ ሁሉ የእግዚአብሄር ቃል ሌላውን ሁሉ እንድንቅ ለእግዚአብሄር ብቻ እንድንሰጥ ያደርጋል፡፡ ንፁህ መንፈሳዊ ምግብ ምልክቱ ለእግዚአብሄር ይበልጥ ለመሰጠት አቅም ይጨምራል፡፡ ንፁህ ምግብ የተመገበ ሰው ለእግዚአብሄርና ለእግዚአብሄር ብቻ ለመኖር ይወስናል፡፡

የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ዕብራዊያን 12፡15-16

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሄር #አስተማሪ #ቃልኪዳን #መልካምትምህርት #ጤንነት #ንፁህ #ትኩረት #ትህትና #አንድነት #ዘላለም #አትለፍ #ትምህርት #ጤና #ፍሬ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አትጨነቁ  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on November 27, 2017, in word. Bookmark the permalink. Comments Off on ጤናማ ያልሆነ ምግብ – ጤናማ ያልሆነ ህይወት.

Comments are closed.

%d bloggers like this: