አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል

sky_without_sun.jpgሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። ኢዮብ 42፡2

እግዚአብሄር ካሰበ ያደርገዋል፡፡ በእግዚአብሄር ሃሳብ ፊት መቆም የሚችል ምንም ሃያል ነገር የለም፡፡ የእግዚአብሄርን ሃሳብና አላማ የሚያቆም ማንም ሃይል የለም፡፡ የእግዚአብሄር አላማ ከሰይጣን ታላቅ እንቅፋት ይበረታል፡፡

በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ። ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን፥ ከሩቅም አገር ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጠራዋለሁ። ተናግሬአለሁ እፈጽምማለሁ፤ አስቤአለሁ አደርግማለሁ። ኢሳያስ 46፡10

እግዚአብሄር ሃሳቡን ማድረግ ይችላል፡፡ ሃሳቡን እንዴት እንደሚፈፅመው እግዚአብሄር ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር ያሰበውን ለማድረግ በማንንም እርዳታ ላይ አይደገፍም፡፡

በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ። መዝሙር 135፡6

እግዚአብሄር ካሰበ ሆነ ማለት ነው፡፡

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፥ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል። ኢሳያስ 14፡24

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ሃይል #ዘላለም #አላማ #እቅድ #ምክር #ጥበብ #የእግዚአብሄርመንግስት #ንጉስ #ሃያል #ሁሉንቻይ #አምላክ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on November 8, 2017, in Authority. Bookmark the permalink. Comments Off on አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል.

Comments are closed.

%d bloggers like this: