ክርስቶስም በልባችሁ እንዲኖር

cloakoflove11.jpgበመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥ኤፌሶን 3፡16-17

በክርስትና ውጤታማ ከሚያደርገን ነገር አንዱ ክርስቶስ በልባችን እንደሚኖር ማወቅ እና ሁልጊዜ ንቁ መሆን ነው፡፡ ክርስቶስ በልባችን እንዳለ ካወቅን እንደሚመራን እናውቃለን፡፡

በአዲስ ኪዳን የብሉይ ኪዳንን አትቅመስና አትንካ ትእዛዝ አንከተልም፡፡

ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት። አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና። ቆላስይስ 2፡20-22

በአዲስ ኪዳን በአእምሮዋችን ክፉና ደጉን በመለየት ብቻ በአእምሮዋችን አንመራም፡፡

እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። ዘፍጥረት 2፡16-17

በምድር በመመላለስ አለምን ያሸነፈው ኢየሱስ በእኛ እያንዳንዳችን ውስጥ በመኖር እኛን በመምራትና በማበርታት አለምን ማሸነፍ ይፈልጋል፡፡

በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ። ዮሃንስ 16፡33

አንድ ሰባኪ ሲናገር ኢየሱስ የተራራውን ስብከት የሰበከው እሱ በምድር ላይ ስጋ ለብሶ የሰራውን ስራ በእኛ በእያንዳንዳችን ውስጥ በመኖር እንደሚደግመው እየተናገረ ነበር ብሎዋል፡፡

በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5

ክርስቶስ በእኛ የሚኖረው ሃይል ሊሆነን ነው፡፡ ክርስቶስ በእኛ የሚኖረው ለእግዚአብሄር አላማ ብቁ ሊያደርገን ነው፡፡

ኢየሱስ በእኛ ውስጥ የሞኖረው ሊመራን ነው፡፡ በውስጣችን መለኮታዊ ህይወት ይኖራል፡፡ በውስጣችን ያለው ኢየሱስ አንድ ነገር ለማድረግ ሲነሳሳ አንብረነው እንንነሳለን፡፡ በውስጣችን ያለው ኢየሱስ አንድን ለማድረግ ካልፈለገ እኛም አንፈልግም፡፡ በውስጣችን ያለው ኢየሱስ ከሮጠ አብረነው እንሮጣለን፡፡ በውስጣችን ያለው ኢየሱስ ከቆመ አብረነው እንቆማለን፡፡

እኛ ለራሳችን ፈቃድ ሞተናል፡፡ አሁን የምንኖረው ኑሮ በውስጣችን ባለው ኢየሱስ አሰራር ላየ በመታመን የምንኖረው ኑሮ ነው፡፡ አሁን ያለን ኑሮ በውስጣችን ያለውን ኢየሱስ ታምነን በመከተል የምንኖረው ኑሮ ነው፡፡

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። ገላትያ 2፡20

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #በመንፈስመመላለሰ #ቃሉንማሰላሰል #መንፈስበእኛ #ህግንመፈፀም #ኢየሱስ #ቤተመቅደስ #ባህሪ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሔርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት #መሪ #መንፈስቅዱስ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on October 7, 2017, in Vision and Leading. Bookmark the permalink. Comments Off on ክርስቶስም በልባችሁ እንዲኖር.

Comments are closed.

%d bloggers like this: