ዋጋ እንዲሰጥ

32584-praying-hands-3-1200.1200w.tn.jpgወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ሰዎች አሰሪን ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች በጥሩ ሁኔታ ስራን ሰርተውለት ጥሩ የሚከፍላቸውን አሰሪ ተግተው ይፈልጋሉ፡፡ ሰዎች ዝነኛ ስም ያለው የተከበረ መስሪያ ቤት ሲሰሩ ይበልጥ ደስ ይላቸዋል፡፡

ሰራተኛንና አሰሪን የሚያገናኝ የሰው ሃይል አስተዳደር ኢንዱስትሪ ትልቅ ኢንዱስትሪ ነው፡፡ ትልልቅ ድርጅት ያላቸው ሰዎች ለድርጅታቸው በቋሚነት ሰራተኛ የሚመለምሉበትና የሚቀጥሩበት ትላልቅ መምሪያ አላቸው፡፡

ድርጅቶቹ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ የሚሰራላቸው ብቁ የሆነው ሰው ለመመልመል ሌት ተቀን ይሰራሉ፡፡ ሁሉም ግን የሚሰራላቸውን ሰው ነው የሚፈልጉት፡፡

ፈልጉኝና ዋጋን እሰጣችኋለሁ ያለ ሰው ሰምቼ አላውቅም፡፡ ስለፈለግነው ብቻ ዋጋን የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለሚፈልጉት ዋጋን ይሰጣል፡፡

ሲፈልጉት ዋጋ የሚሰጣቸው ሰዎች መመዘኛ ደግሞ ሰው መሆን ነው፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም። ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡26-28

ሲፈልጉት ዋጋ የሚሰጣቸው ሰዎች መመዘኛ ደግሞ በእምነት መፈለግ ነው፡፡

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

እምነት ደግሞ የሚመጣው የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ነው፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ሲፈልጉት ዋጋ የሚሰጣቸው ሰዎች መመዘኛ ደግሞ በፍፁም ልብ መፈለግ ነው፡፡

እግዚአብሔር ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ኩሩ ነው፡፡ እግዚአብሔር ማንም ባጣ ቆየኝ እንዲያደርገው አይፈቅድም፡፡ እግዚአብሔርን በሁለት ሃሳብ እንድንፈልገው አይፈልግም፡፡ እግዚአብሔርን ፈልገን እንደባለጠግነቱ መጠን ዋጋ እንዲሰጠን ካስፈለገ በፍፁም ልባችን ልንፈልገው ይገባል፡፡

እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ኤርሚያስ 29፡13

ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ  1፡7-8

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ይህ አዲስ ዓመት እግዚአብሔርን በመፈለግ እንደባለጠግነቱ መጠን ከእግዚአብሔር ዋጋ የምንቀበልበት ዓመት ይሁን፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ማየት #እግዚአብሔርንመፈለግ #መፀለይ #ፍፁምልብ #አዲስአመት #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on September 9, 2017, in Prayer, Reward. Bookmark the permalink. Comments Off on ዋጋ እንዲሰጥ.

Comments are closed.

%d bloggers like this: