ሰዎችን አጥማጆች

anthias-fish-1080p-hd-wallpaper.jpgእርሱም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። ማቴዎስ 4፡19

ኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያታችንን እዳ በመክፈሉ የእግዚአብሄር ቁጣ በእኛ ላይ አይኖርም፡፡ ኢየሱስን አዳኛችንና ጌታችን አድርገን በመቀበላችን ከጥፋት ድነናል የዘላለም ህይወት አግኝተናል፡፡

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36

ሰዎችን የማጥመድ ታላቅ ሃላፊነት ባይኖርብን ኖሮ ወዲያው እንደዳንን እግዚአብሄር በሰበሰበንና በዚህም ምድር እንድኖር ባልፈለገ ነበር፡፡ በዚህ ምድር የቆየነው ሌሎችን የማጥመድ ሃላፊነትን ተሸክመን ነው፡፡

በምድር ላይ ስንኖር ይህን ሰዎችን የማጥመድ አላማን ይዘን ነው የምንኖረው፡፡ በምድር የምንኖረው ይህንን ሰዎችን የማጥመድ ሸክም ተሸክመን ነው፡፡ በምድር የምንኖረው በአስተሳሰባችን በአነጋገራችንና በአደራረጋችን ይህንን ታላቅ ተልእኮ ለማሳካት ነው፡፡

ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡ 10-12

በውጭ ካሉት ጋር ስንኖር አነጋጋራችንና አካሄዳችን እነርሱን ለክርስቶስ ለማጥመድ ንስሃ እንዲገቡና ከእግዚአብሄር ጋር እንዲታረቁ የታቀደ መሆን ይገባዋል፡፡

ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን። ቆላስይስ 4፡5-6

ራሳችንን በመግዛት ፣ እግዚአብሄርን በነገር ሁሉ በማመስገንና ባለማጉረምረም በአለም እንደ ብርሃን እየታየን ብዙዎችን የማጥመድ እድል በእጃችን ነው፡፡

በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤ በእነርሱም መካከል የሕይወትን ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፥ ፊልጵስዩስ 2፡14-16

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #አጥማጆች #ብርሃን #ጨው #ምስክር #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on May 27, 2017, in evangelism. Bookmark the permalink. Comments Off on ሰዎችን አጥማጆች.

Comments are closed.

%d bloggers like this: