በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልም

rock.jpgለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡8

በእግዚአብሄርና ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥረናል፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የምንኖረው በእግዚአብሄር ህግ በእግዚአብሄር ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ለእግዚአብሄር ህግ አንሰጠውም፡፡ እኛ በእርሱ ጥላ ስር እንገባለን እንጂ እርሱ በእኛ ጥላ ስር አይገባም፡፡ እግዚአብሄር ንጉስ ነው፡፡

በምድር ለይ ተቋቁመን ለመኖር የእግዚአብሄርን ሃሳብ ማግኘት አለብን፡፡ የምንከናወነው የእግዚአብሄርን ቃል እውነት ስናገኝ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር እውነት ደግሞ ለራሱ ይቆማል፡፡ የእግዚአብሄርን እውነት ለማቆም የምንረዳው ምንም ነገር የለም፡፡

የመጨረሻው ማድረግ የምንችለው መልካምና የተሻለ ነገር በዚህ እውነት መተገን ነው፡፡ በዚህ እውነት የምንተገነው ለራሳችን ብለን ነው፡፡ ከእውነት ጋር የምንቆመው እውነትን ለመደገፍ ሳይሆን ለራሳችን ለመጠለል ብለን ነው፡፡

ከቃሉ እውነት ጋር የምንወግው እውነትን ደግፈን ለማቆም አይደለም፡፡ የቃሉ እውነት ደግፎ የሚያቆመው ማንንም ሰው አይፈልግም፡፡ በእውነት ላይ ተነስቶ የሚቋቋም ሰው የለም፡፡ በምድር ላይ ያለው ታላቁ ሰው እንኳን ለቃሉ እውነት እንጂ ከእውነት ተቃርኖ መዝለቅ አይችልም፡፡

የአዲስ ኪዳን አገልጋይ የነበረው ሃዋሪያው እንኳን በዚያ ሁሉ ክብሩ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ እንችልም ይላል፡፡ በእውነት ላይ ምንም ሊያደርግ የሚችል ሰው ከሰማይ በታች የለም፡፡

እጅግ ጠቢብ የሆነ ሰው ሊያደርግ የሚችለው ብልህ ነገር ለእውነት መቆም ነው፡፡ እጅግ የተሻለ ነገር የሚያደርገው ሰው ሊያደርግ የሚችለው በእውነት መጠለል ነው፡፡

ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡8

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እውነት #ቃል  #ውሸት #ሀሰት #ሰይጣን #ዲያቢሎስ #ጠላት #ማታለል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on May 19, 2017, in truth. Bookmark the permalink. Comments Off on በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልም.

Comments are closed.

%d bloggers like this: