የእውነት ጦር መሳሪያ

belt of truth.jpgሰይጣን ከመጀመሪያ ጀምሮ የሰው ልጆችን የሚያጠቃው በውሸት ነው፡፡ ሰይጣን ወደሄዋን መጥቶ ያታለላት እግዚአብሄር ከበላችሁ ትሞታላችሁ ያለውን አትሞቱም ብሎ በመዋሸት ነበር፡፡

ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡3

የሰይጣን መስረቂያ ማረጃና ማጥፊያ መሳሪያው ውሸትን እንድንቀበልና ግራ እንድንጋባ ማድረግ ነው፡፡

ሰይጣን ህይወታችንን እንዳይበዘብዘው እውነትምን መፈለግ ፣ እውነትን ማሰብ ፣ እውነትን መናገርና እውነትን መኖር ይገባናል፡፡

እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። ዮሃንስ 8፡32

ኢየሱስ ሰይጣንን በመስቀል ላይ አሸንፎታል፡፡ ኢየሱስ ሰይጣንን ያሸነፈው ለእኛ ነው፡፡ እውነት በሰይጣን ላይ ያለንን ድል የምናፀናበት መንገድ ነው፡፡ በእውነት ወገባችንን መታጠቅ በሰይጣንን ላይ ያለንን ድል የምናስከብርበት መንገድ ነው፡፡ እውነት በሰይጣን ላይ ውጤታማ የጦር መሳሪያ ነው፡፡ እውነትን ስናስበው ስንናገረውና ስናርገው ሰይጣን በህይወታችንና በሚሰሙን ህይወት ስልጣኑን ያጣል፡፡

እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ ኤፌሶን 6፡14-15

እውነት የሌለው ሰው ራሱን መግዛት አይችልም፡፡ እውነት የሌለው ሰው ቆፍጠን ማለት አይችልም፡፡ የእግዚአብሄር ቃል እውነት የሌለው ሰው በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል፡፡ ማቴዎስ 13፡21

እውነትን የሚያውቅ ሰው በህይወቱ ያለውን የእግዚአብሄርን አላማ ከመፈፀም መብዛት ይሁን መጉደል አያግደውም፡፡

ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፊልጵስዩስ 4፡11-13

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ውሸት #ሀሰት #ሰይጣን #ዲያቢሎስ #ጠላት #ማታለል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on May 18, 2017, in truth. Bookmark the permalink. Comments Off on የእውነት ጦር መሳሪያ.

Comments are closed.

%d bloggers like this: