እጅግ ኃይል ታደርጋለች – ሰበብ የለንም

power plug.jpgየጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች። ያዕቆብ 5፡16-18

የፃድቅ ሰው በኢየሱስ የሚያምን ሰው ፀሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች፡፡ በኢየሱስ የመስቀል ስራ ከእግዚአብሄር ጋር የታረቀ ሰው ፀሎት ስራዋ ሃያል ነው፡፡

እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ ሮሜ 3፡22

ኢየሱስ ከሙታን እንደተነሳ የሚያምን ሰው ፀሎት እጅግ ውጤታማ ነው፡፡

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10

የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል። ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ፤ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ተኩል ዝናብ አልዘነበም። እንደ ገናም ጸለየ፤ ዝናብም ከሰማይ ዘነበ፤ ምድርም ፍሬዋን ሰጠች። ያዕቆብ 5፡16-18 ህያው ቃል (መደበኛ ትርጉም)

The earnest prayer of a righteous man has great power and wonderful results. James 5፡16 Living Bible (TLB)

የጻድቅ ሰው ልባዊ ጸሎት ታላቅ ኃይል እና አስደናቂ ውጤት አለው፡፡ (ህያው ቃል)

የኤልያስ ፀሎት ትልቅ ሃይል የነበረው አስደናቂ ውጤት ያመጣው ኤልያስ መልአክ ስለነበረ አይደለም፡፡ ኤልያስ እንደ እኔና እንደ እናንተ ሰው ነበረ፡፡ ኤልያስ ከልቡ አጥብቆ ፀለየ፡፡

በፀሎታችን ታላቅ ሃይል ላለማምጣት ምንም ሰበብ የለንም፡፡ እግዚአብሄር እንድናሸንፍበት የሰጠንን ይህን ታላቅ ሃይል በሚገባ እንጠቀምበት፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አጥብቆ #ፀሎት #ልመና #ኤልያስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሃይለ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ምስጋና

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on March 24, 2017, in Prayer. Bookmark the permalink. Comments Off on እጅግ ኃይል ታደርጋለች – ሰበብ የለንም.

Comments are closed.

%d bloggers like this: