ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል

pregnantአንተ ተነሥ ጽዮንንም ይቅር በላት፥ የምሕረትዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና፤ መዝሙር 102:13

እነርሱም፦ ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል ለመውለድም ኃይል የለም። ኢሳይያስ 37፡3

እግዚአብሄር በህይወታችን ሊሰራ ያለውን ነገር ማወቅ ልጅን እንደመፀነስ ነው፡፡ የራእዩ ዘር አንድ ሃሳብ ሊሆን ይችላል፡፡ ዘሩ በልባችን ይዘራል ጊዜ ወስዶ ይዳብራል ያድጋል፡፡

ራእዩ የሚፈፀምበት ጊዜ ሲደርስ ይወለዳል፡፡ ሴት ያረገዘችውን ልጅ በብዙ ምጥና ህመም እንደምትወልደው እንዲሁ ራእይ በብዙ ምጥና መማለድ ይወለዳል፡፡

አንዲት ሴት ልጅ የምትወልድበት ጊዜ ስለደረሰ ብቻ አትወልድም፡፡ የመውለድ የራሱ ሂደቶች አሉት፡፡ መጀመሪያ ህመም ይሰማት ይጀምራል፡፡ ህመም ይሰማት ጀመር ማለት ወዲያው ትወልደዋለች ማለት ግን አይደለም፡፡ የየመጀመሪያው ህመም የምጥ መጀመሪያ ማለት ነው፡፡

ስለምጥና ክርስቲያን ዶክተር ስታስረዳ የሰማሁትን ላካፍላችሁ፡፡ በምጥ መጀመሪያ ሴት ማድረግ ያለባት ምጡን መታገስ ብቻ ነው፡፡  ምክኒያቱም የመጀመሪያው የህመም ስሜት የምጥ መጀመሪያ ብቻ ነው፡፡ ይህንን አሰራር የማይረዱ ሴቶች ልክ መጀመሪያ ምጥ እንደተሰማቸው በፍጥነት መውለድ ይፈልጋሉ፡፡ ህመሙን መታገስ ስለማይፈልጉ መግፋት ይጀምራሉ፡፡ እውነት ነው ጊዜው ሲደርስ መግፋት ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያው ህመም ትክክለኛው የመግፊያ ጊዜ አይደለም፡፡

የተፈጥሮ አሰራር ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የምጥ ህመም የተሰማት ሴት ማድረግ የምትችለው የተሻለ ነገር ምጡን መታገስ ብቻ ነው፡፡ ምጡን እየታገሰች በቆየች ቁጥር ሰውነትዋ እየተከፈተ ይሄዳል፡፡ ሰውነትዋ የሚገባውን ያህል ሲከፈት  ብቻ ነው መግፋት ያለባል፡፡ በዚያን ጊዜ የምትገፋበት ሃይል ልጁ እንዲወለድ ያደርገዋል፡፡ ከዚያ በፊት የምትገፋው ግን እርስዋ እንድትደክም ያደርጋታል ልጁም እንዲወለድ ምንም የሚጠቅመው ጥቅም የለም፡፡

በራእይም አንደዚሁ ነው፡፡ የራእይ ዘር በውስጣችን አለ ማለት ራእዩ አሁን ይፈፀማል ማለት አይደለም፡፡ ራእዩ የሚወለድበት ጊዜ ደግሞ አለ፡፡ ራእዩ የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ ህመምና ማማጥ ይሆናል፡፡ የራእዩ መፈፀሚያ ጊዜ ሲደረስ በጸሎትና በምልጃ ራእዩ ይፈፀማል፡፡

የበረሃ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋላይቱስ የምታምጥበትን ጊዜ ትመለከታለህን?እርስዋ የምትፈጽመውንስ ወራት ትቈጥራለህን? የምትወልድበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? ይንበረከካሉ፥ ልጆቻቸውንም ይወልዳሉ፥ ከምጣቸውም ያርፋሉ። ኢዮብ 39፡1-3

ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና። እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ሮሜ 8፡22፣26

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ #ፀሎት #እግዚአብሄርንመፈለግ #ማማጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #አላማ #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መቃተት #መንበርከክ #መጠበቅ #ትግስት #መሪ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on March 15, 2017, in Prayer. Bookmark the permalink. Comments Off on ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል.

Comments are closed.

%d bloggers like this: