ክፍት የስራ ቦታ ለሁሉም

Publication1.jpgየእግዚአብሄር መንግስት ከዚህ ቀጥሎ በተመለከተው ክፍት የሥራ መደብ አመልካቾችን በቋሚነት መቀበል ይፈልጋል፡፡

የስራ መደቡ መጠሪያ፡ እግዚአብሄርን መፈለግ

የሚፈለግ የሰው ብዛት፡ ያልተወሰነ

መመዘኛ፡ ማንም ሰው

የስራው ሁኔታ፡ በቋሚነት

ተፈላጊ ችሎታ፡

  • በእምነት የሚፈልገው

ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ 1፡6-8

  • ትጋት ያለው እስከሚከፈት የሚያንኳኳ

የደሞዝ ደረጃ፡ በእግዚአብሄር ዋጋ አከፋፈል ደረጃ መሰረት

ይህ የስራ ማስታወቂያ እስከ ኢየሱስ ዳግም ምፃት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ እርግጥ ነው እኛ እስከዚያ በህይወት ከቆየን ማለት ነው፡፡

አመልካቾች ባላችሁበት ቦታ በማንኛውም ሰከንድ እግዚአብሄርን በመፈልግ በትጋት ለሚፈልጉት ዋጋ በሚሰጠው በእግዚአብሄር አሰራር ተጠቃሚ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #እግዚአብሄርንመፈለግ #አለማየት #ቃል #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on March 13, 2017, in evangelism. Bookmark the permalink. Comments Off on ክፍት የስራ ቦታ ለሁሉም.

Comments are closed.

%d bloggers like this: