ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም

man_carrying_huge_rock.jpgትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም። 1ኛ ዮሐንስ 5፡3

እግዚአብሄር የሚያደርገውን ነገር ሁሉ የሚያደርገው በእቅድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለስራው ጨካኝ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለመዝናናትና ለጫወታ የሚያደርገው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር የሚያደርገውንብ ሁሉ የሚያደርገው ከልቡ ነው፡፡

ከእኛም ጋር ባለው ግንኙነት በከንቱ የሚያደርገው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ይህን አድርጉ ካለ ያንን እንድናደርግ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በቃሉ እንድንፈፅመው ካዘዘው ነገር ለሙከራ ወይም ለወግ የተፃፈ ቃል የለም፡፡ በቃሉ እንድናደርገው የተፃፈው ሁሉ ማድረግ እንደምንችል እግዚአብሄር ያውቃል፡፡

እግዚአብሄር የፍቅር አምላክ ነው፡፡ በቃሉ ያዘዘው ሁሉ የምናደርገው በፍቅር ነው፡፡ በፍቅር ቃሉን እንፈፅማለን፡፡ በፍቅር ቃሉን እንታዘዛለን፡፡ በፍቅር ቃሉን እናደርገዋለን፡፡

የእግዚአብሄር ትእዛዞች ሰው በፍቅር ሊያደርጋቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ የእግዚአብሄር ትእዛዛት ከሰው አቅም በላይ አይደሉም፡፡ የእግዚአብሄር ትእዛዞች ማንም የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ሊያደርጋቸውና ሊፈፅማቸው የሚችላቸው ናቸው፡፡ ትእዛዞቹ በውስጣችን ከሚሰራው የሚያስችል ሃይል ወይም ፀጋ ችሎታ በላይ አይደሉም፡፡ ትእዛዞቹ ከተቀበልነው የፍቅር ጉልበት በላይ አይደሉም፡፡ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም፡፡

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ቃል #መታዘዝ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #የእግዚአብሄርፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መስተዋት #መፅሃፍቅዱስ #ነፃነት  #እምነት #መስማት #መከተል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on March 1, 2017, in word. Bookmark the permalink. Comments Off on ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም.

Comments are closed.

%d bloggers like this: