እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም!

46879143-amazing-pictures.jpgይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።  ዘዳግም 33፡26

እግዚአብሄር በሰማይ ላይ ያለው ህዝቡን ሊረዳ ነው፡፡ እግዚአብሄር ስራው ለክብሩ የፈጠረውን ህዝብ መርዳርትት ነው፡፡ እግዚአብሄር ስራው እኛን መከታተል ነው፡፡ የእግዚአብሄር ስራ እኛ ልጆቹ ምንም እንደማይጎድልብን እርግጠኛ መሆን ነው፡፡ እግዚአብሄር በሰማያት ላይ የሚሄደው ሊረዳህ ነው፡፡

እግዚአብሄር በሰማያት ላይ ያለው እኛን ሊረዳን ነው፡፡ እግዚአብሄር ከፍ ብሎ ያለው እኛን በትክክል ለማስተዳደር ነው፡፡ እግዚአብሄር በጥበብ በሃይልና በፍቅር አለምን ሊገዛ በደመናት ላይ አለ፡፡ ከእግዚአብሄር ቁጥጥር ውጭ የሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር የማያውቀው ነገር በምድር ላይ አይፈፀምም፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስደንቀው ነገር “እንዴ!” የሚያሰኘው ነገር የለም፡፡ የእግዚአብሄር ማስተዋል አይመረመርም፡፡

አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳያስ 40፡28

ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ በአሕዛብና በአምላኮቻቸውም ፊት ከግብጽ በተቤዠው ሕዝብ ፊት ተአምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ሄደለት እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ? 2ኛ ሳሙኤል 7፡23

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሄርታላቅ #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #መዳን #ማድረግ #መስዋእት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on February 5, 2017, in worship. Bookmark the permalink. Comments Off on እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም!.

Comments are closed.

%d bloggers like this: