መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም

o-rest-facebookየኢየሱስን የፀሎት ፍሬ ያየ ከደቀመዛሙርቱ አንዱ ኢየሱስን እንጸልይ ዘንድ አስተምረን ብሎ ጠየቀው፡፡ እውነትም ኢየሱስ ፀሎትን በሙሉ ፍሬያማነት የተጠቀመበት ነበር፡፡ ኢየሱስ የፀሎት ሰው ነበር፡፡ እየሱስ ውጤታማን ፀሎት የኖረውም ያስተማረውም ነበር፡፡

እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው። ሉቃስ 11፡1

ኢየሱስ ግን እናንተስ እንዲህ ፀልዩ በማለት ያስተማራቸውን የመጨረሻውን መስመር እንመልከት፡፡

መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን። ማቴዎስ 6፡13

ይህ ማለት ይህን ፀሎት የምንፀልየው በአንተ ሃይል በመተማመን ነው፡፡ መንግስት ያንተ ነው ፣ ሃይልም ያንተ ነው ፣ ክብርም ያንተ ነው ፡፡

አንተ ትችላለህ የሚሳንህ የለም፡፡

ስለዚህ የምንፀልየው በእረፍት ነው፡፡

የምንፀልየው በእምነት ነው፡፡

የምንፀልየው በመተማመን ነው፡፡

ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ ስለፀሎት ሲናገር ከምስጋና ልመናችሁን አስታውቁ የሚለው፡፡

ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ፊልጵስዩስ 4፡6

ፀሎት ለእግዚአብሄር ሃይል እውቅና በመስጠት መሆን ይኖረበታል፡፡ ፀሎታችን ለእግዚአብሄር ቻይነት እውቅና በመስጠት፡፡

ከእረፍት ያልሆነ ፀሎት እግዚአብሄርን አያስደስተው፡፡ በእግዚአብሄር ላይ የማረፍ ፣ በእግዚአብሄር ላይ የመደገፍ ፣ በእግዚአብሄር የመተማመን ፀሎት እግዚአብሄርን ያስደስተዋል፡፡

ፀሎታችን በዚህ መረዳት ነው፡፡ ልመናችን ይህን እውቅና በመስጠይት ነው፡፡ ፀሎታችን በእረፍት በመተማመንና በእምነት ነው፡፡

መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን። ማቴዎስ 6፡13

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፀሎት #ምልጃ #ምስጋና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ደቀመዝመር #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልመና #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እረፍት #መተማመን #እምነት #መደገፍ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on December 10, 2016, in Prayer. Bookmark the permalink. Comments Off on መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም.

Comments are closed.

%d bloggers like this: