የአቋም መግለጫ

n-black-hand-pointing-628x314እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም። ኢሳይያስ 42:8
እግዚአብሄር እንዲህ ይላል ክብሬን ለሌላ ምስጋናዬን ለተቀረፁ ምስሎች አልሰጥም፡፡ እግዚአብሄር ፡፡ ምንም ክርክር እንዳይነሳ እኔ እግዚአብሄር ነኝ ስሜም ይህ ነው በማለት በመጀመሪያ ስሙን ግልፅ አደረገልን፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ክብሩን ለማንም ለማንም እንደማይሰጥ ተናገረ፡፡ ብዙ የሚያጋራው ነገሮች ቢኖሩም ክብሩን ግን ለማንም አይሰጥም፡፡ ከማንም ሰው ጋር እኩል መቆጠር አይፈልግም፡፡
ማንም የሰው ልጅ የእግዚአብሄርን ክብሩን እንዲሸፍን አይፈቅድም፡፡
የእግዚአብሄርን ክብር መውሰድ የስነመለኮት አመለካከት ብቻ ሳይሆን በሰው ልጅ የእለት ተእለት ህይወት ሊከሰት የሚችል የዘወትር ፈተና ነው፡፡ ሰው ካልተጠነቀቀ የእግዚአብሄን ክብር በመውሰድ እግዚአብሄርን ያስቆጣዋል፡፡ አንዳንደ ሰው እኔ ምን ክብር አለፅ ይላል ነገር ግን ሰዎች አንተን አልፈው እግዚአብሄርን ማየት ካቃታቸው ወድቀሃል፡፡ ለእግዚአብሄር የሚገባውን ትኩረት ራስህ ጋር ካስቀረኸው ክብሩን ወስደሃል፡፡ ሰዎች ወደ አንተ ሲያመለክቱ ወደእግዚአብሄር ካላመለከትክ ክብሩ ጣፍጦሃል ማለት ነው፡፡
ኢየሱስ በምድር ላይ ይመላለስ በነበረ ጊዜ ለእግዚአብሄር የሚገባውን ክብር ወደ እርሱ ሲያመጡ የእግዚአብሄርን ክብር ላለውሰድ ይጠነቀቅ ነበር፡፡
ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም። ሉቃስ 18፡19
በበርናባስና በጳውሎስ ታዕምራት በተደረገ ጊዜ ሰዎች ሊያመልኳቸው ሲሞክሩ የእግዚአብሄርን ክብር መውሰድ በጣም ስሱና ሴልሲቲቭ ነገር ስለሆነ ወዲያው ነው ፊት ለፊት የተቃወሙት፡፡ ሰዎች እነርሱን ባከበሩዋቸው መጠን ራሳቸውን አዋረዱ፡፡
ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥ ሐዋርያት 14፡14
የሰዎች ትኩረት ከእነርሱ ላይ ተነስቶ ወደ እግዚአብሄር እንዳይሄድ የሚፈልጉ ለእግዚአብሄር መሰጠት ያለበትን ክብር በተለያየ ምክኒያት ለራሳቸው የሚወስዱ ሰዎችን እግዚአብሄር ይናገራል ክብሬን ለሌላ ለማንም አልሰጥም፡፡
ካልተጠነቀቅን ደግሞ እግዚአብሄር ክብሩ እንደማይገባን የሚያሳይበትና የሚያስታውስበት የራሱ መንገድ እንዳለው ከናቡከደነፆር ታሪክ ልንማር ይገባል፡፡ ዳንኤል 5፡19-21
ንጉሱ የተናገረውን ንግግር አድምጠው ሰዎች ለእግዚአብሄር የሚገባውን ክብር ለሰው ሰጡ፡፡ ችግሩ ሰው ክብሩን መስጠቱ አይደለም፡፡ ችግሩ ግን የተሰጠውን ክብር ለእግዚአብሄር መልሶ አለመስጠቱ ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ክብር እንዳይሸፍን ራሱን አለመደበቁ ነው ችግሩ ፡፡
ሕዝቡም፦ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው የሰውም አይደለም ብለው ጮኹ። ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ። ሐዋርያት 12፡22-23
የእግዚአብሄርን ክብር መውሰድ እኔን አይመለከተኝም የሚል ሰው የለም፡፡ ፍራ እንጂ የትእቢትን ነገር አታስብ፡፡ ራስህን አዋርድ፡፡ ሁልጊዜ ለእግዚአብሄር አምላክነት እውቅና ስጥ፡፡ በምንም ምክኒያት ይሁን የሰዎች ትኩረት አንተ ጋር እንዳይቀር ተጠንቀቅ፡፡ ሰዎች ክብር ሲሰጡህ በተራህ አንተ ለእግዚአብሄር ክብር ስጥ፡፡
እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡31
ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። ሮሜ 11፡36
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር #ትእቢት #ኩራት #እግዚአብሄር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on November 23, 2016, in Character, grace. Bookmark the permalink. Comments Off on የአቋም መግለጫ.

Comments are closed.

%d bloggers like this: