ምርጫን ማስተካከል

electionአሜሪካን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት ከተወዳደሩት እጩዎች መካከል ሁለቱ ፓርቲያቸውን ወክለው ለመጨረሻው የምርጫ ቀን ደርሰዋል፡፡
እያንዳንዱም አሜሪካዊ ደግሞ የወደፊቱን ለማስተካከልና አደጋ ላይ ላለመውደቅ ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ ይሻለኛል ያለውን እጩ ተወዳዳሪ ይመርጣል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ላይ እንዳለው ተፅእኖ የሚያክል ወይም ትንሽ እንኳን የሚጠጋ ተፅእኖ ሊያደርግ የሚችል ምንም ፖለቲከኛ የለም፡፡ በምድር ያሉ ፖለቲከኞች በህይወታችን ላይ ታላቅ ተፅእኖ ለማምጣት በጣም ውስን ናቸው፡፡
መፅሃፍ ስለእግዚአብሄር ተፅእኖ ሲናገር እንዲህ ይላል
አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል። ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች። እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል። እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል። ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡3-8
ከእግዚአብሄር በስተቀር ህይወታችንን ሊለውጥ የሚችል ምንም ፖለቲከኛ የለም፡፡ ሁል ጊዜ ልንፈልገው የሚገባው ጌታ እግዚአብሄርን ነው፡፡ የማንም ፖለቲካኛ ሃሳብ ከእግዚአብሄር ሃሳብ በላይ ሊገዝፍብን አይገባም፡፡ ለየትኛውም ፖለቲከኛ ያለን መሰጠት ለእግዚአብሄር ያለንን መሰጠት ቅንጣት ያህን እንኳን ሊቀንሰው አይገባም፡፡ ሃገራችንን የሚመራውን ሰው መምረጥ ጥቅም አለው፡፡
ከምንም ምድራዊ ምርጫ ሁሉ በላይ እጅግ ጠቃሚ ምርጫ እግዚአብሄር ለመዳኛችን ያዘጋጀውን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል መምረጥ ነው፡፡ በህይወት ዘመናችን መምረጥ ያለብን እጅግ በጣም ወሳኝ ምርጫ የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስቱን መፈለግ ነው፡፡
ሃገርን በፕሬዝዳንትነት የሚመራውን ሰው ለመምረጥ ያለ የምርጫ ሃላፊነት በህይወታችን መምረጥ ካለብን ምርጫ ጋር በፍፁም አይገናኝም፡፡ በህይወት ዘመናችን መወሰን ያለብን ይህ ውሳኔ ከምንም የበለጠ ጥቅምና ጉዳት ያለው ውሳኔ ነው፡፡ የምርጫ ውሳኔያችን ውጤት የምድር ኢኮኖሚያችንንና ደህንነታችንን ብቻ ሳይሆን የዘላለም እጣ ፈንታችንን የሚወስን ነው፡፡
እግዚአብሄር እየሱስን ወደ ምድር ሲልከው ለሃጢያታችን እንዲሞትና በመስቀል ላይ የሃጢያታችንን እዳ እንዲከፍል ነው፡፡
ይህንን እየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለውን የሃጢያት ዋጋ ለእኔ ነው ብሎ የሚቀበልና እየሱስን የሚመርጥ የዘላለም ህይወት ያገኛል፡፡ እግዚአብሄርን ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ የማይቀበል ለዘለአለም ከእግዚአብሄር በመለየት የዘላለም ፍርድ ያገኘዋል፡፡ በምድር ላይ እየሱስን የሚመርጡና የእግዚአብሄር ልጅነትን ስልጣን የሚቀበሉ አሉ፡፡ በምድር ላይ እስከ መጨረሻው እየሱስን የማይመርጡ ሰዎች ደግሞ አሉ፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ኢየሱስ #ጌታ #ምርጫ #ምስክር #ፀጋ #ምናን ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on November 8, 2016, in Uncategorized. Bookmark the permalink. Comments Off on ምርጫን ማስተካከል.

Comments are closed.

%d bloggers like this: