መሰረተ እምነት

foundation-sky-sm ከእግዚአብሄር ጋር ለአለን ግንኙነት እምነት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ያለእምነት እግዚአብሄን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡ ካለእምነት እግዚአብሄርን ልንይዘውም ፣ ከእግዚአብሄር ልንቀበልም ሆነ ከእግዚአብሄር ጋር ልንራመድ አንችልም፡፡
በመጀመሪያ ኢየሱስን የህይወታችን አዳኝና ጌታ አድርገን ለመቀበል እምነት ያስፈልጋል፡፡ ኢየሱስ በመስቀል እኛን ተክቶ እንደሞተ እና እንደተነሳ ማመን ይጠበቅብናል፡፡
በምድር ላይ እንደ ልጅ የእግዚአብሄርን ስራ ሰርተን ለማለፍ ለኑሮ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ እግዚአብሄር እንደሚያቀርብና እንደሚያዘጋጅልን ማመን አለብን፡፡ ክርስቲያን ከኑሮ ፍርሃት መውጣት ካልወጣ በስተቀር ለእግዚአብሄር መኖርም ሆነ እግዚአብሄርን ማገልገል ያቅተዋል፡፡
እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡31፣33
ሰው ስለብዙ ነገር እግዚአብሄርን ማመን ይፈልጋል፡፡ ሰው የሚያስፈልገው ዋናው ነገር ግን እግዚአብሄርን ለመሰረታዊ ፍላጎቱ ማመን ነው፡፡ ሰውን በአብዛኛው የሚይዘው የእግዚአብሄርን ፅድቅና መንግስትን በነፃነት እንዳይፈልግ የሚያንቀው እግዚአብሄርን ለሚበላው ለሚለብሰውና ለመሳሰሉት አለማመን ነው፡፡
ሰው ከድህነት ፍርሃት ነፃ ከወጣ ለእግዚአብሄር የሚጠቅም የክብር እቃ ይሆናል፡፡ ሰው ግን በኑሮ ፍርሃት ከታሰረና እግዚአብሄር የእርሱን መሰረታዊ ፍላጎት እንደሚያሟላ ከልቡ ካላመነ እግዚአብሄር የሚፈልገውን ኑሮ ሊኖር እግዚአብሄርንም ሊያገለግል አይችልም፡፡
የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል። ማርቆስ 4፡19
ስለ መሰረታዊ ፍላጎቱ ጌታን ማመን መሰረታዊ የእምነት ደረጃ ነው፡፡ ሰው ስለብዙ ነገር እግዚአብሄርን አምናለሁ ቢል ስለመሰረታዊ ፍሎላጎቱ ጌታን ካላመነ እምነቱ መሰረት የለሽ እምነት ነው፡፡ ሰው ለመሰረታዊ ፍላጎቱ እግዚአብሄርን ካመነ ደግሞ እግዚአብሄር እንደሚለው መኖርና በነፃነት ኢየሱስን መከተል ይችላል፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on October 22, 2016, in Uncategorized. Bookmark the permalink. Comments Off on መሰረተ እምነት.

Comments are closed.

%d bloggers like this: