እውነተኛ ትህትና

Talking from the heart Blog

7a9915bb2774378c0c0035704e52fd73ከእግዚአብሄር ጋር ለመኖርና አሸናፊ ለመሆን ትህትና እጅግ አስፈላጊ ባህሪ ነው፡፡ ካለ ትህትና ከእግዚአብሄ ጋር እጣላለን ፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ ወገን አይሆንም ፡፡ እንዲያውም እግዚአብሄር ትዕቢተኛውን ይቃወማል፡፡
ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ። ያዕቆብ 4፡6
ትህትና ይህን ያህል አስፈላጊ ከሆነ ትህትና ግን ምንድነው ብለን መጠየቅ ጥበብ ነው፡፡ ትህትናን በደንብ ልንማረውና ልናጠናው ተግተንም ልንለማመደው የሚገባ የተወደደ ባህሪ ነው፡፡ ሰዎች ትህትና ብለው የሚያደርጉዋቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እውነተኛ ትህትና ግን ምንድነው፡፡
  • · ትህትና ለሁሉም ሰው ያለ አክብሮት ነው፡፡ ትሁት ሰው ለወገኔ ይጠቅማል በማለት አንዱን ከሌላው ሰው በወገናዊነት አያበላልጥም፡፡ ትሁት ሰው ለሁሉም ከፍ ያለ አክብሮት ያለው ሰው ሲሆን ሁሉንም ለማገልገልና ለመጥቀም የተዘጋጀ ነው፡፡
ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ፊልጵስዩስ 2፡3
  • · ትሁት ሰው ሌላው ሰው ከእርሱ እንደሚሻል በቅንነትና በእውነት የሚያምን ነው፡፡ ትሁት ሰው ራሱን ብቻ አስፈላጊ አድርጎ የማይመለከት ሰው ነው፡፡ ትሁት ሰው የሰውን ሁሉ አስፈላጊነት የሚረዳ ሰው ነው፡፡ ትሁት ሰው በሌላው ሰው ስጦታ…

View original post 459 more words

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on October 15, 2016, in Uncategorized. Bookmark the permalink. Comments Off on እውነተኛ ትህትና.

Comments are closed.

%d bloggers like this: