ስድስቱ የፆም በረከቶች

fasting-immune-systemፆም በጣም ጠቃሚ የክርስትና ህይወት ክፍላችን ነው፡፡ ፆም በእግዚአብሄር ነገር ላይ ለማተኮር የስጋችንን ፍላጎት የምናዘገይበት መንገድ ነው፡፡ ከምግብ መብላት ጋር ተያይዘው የሚመጡትን የሰውነት ክብደትና መጫጫን በማስወገድ ቀለል ብሎን በእግዚአብሄር ፊት ለመፀለይ ያስችለናል፡፡
ፆም በብርድ ጊዜ የምንለብሳቸውን ለመሮጥም ሆነ እንደልብ ለመንቀሳቀስ የሚያስቸግሩትን ከባባድ ልብሶች እንደማውለቅ ነው፡፡ ፆም ለመንፈሳዊ ህይወታችን ማደግና ለህይወታችን መለወጥ ከፋተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ከፆም ጥቅሞች መካከል፡-
· ስጋን ለመጎሸም የእግዚአብሄርና የመንፈስ ነገር ለስጋ ሞኝነት ነው፡፡ ስጋዊ ባህሪያችን እግዚአብሄርን አይፈልግም፡፡ ስጋን የምንጎሽምበት አንዱ መንገድ መፆም ነው፡፡ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ . . . ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ። 1ኛ ቆሮንጦስ 9፡25፣27
ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ። ሮሜ 13፡14
· ለእግዚአብሄር መንፈስ ይበልጥ ንቁ ለመሆን
ሰውነታችን የምግብ መፈጨትን የሚያካሂደው እንደ ፋብሪካ ነው፡፡ ምግብ ስንበላ ሰውነታችን በከባድ ስራ ላይ ይጠመዳል፡፡ ስለዚህ ነው እንዳንዴ ከባድ ምግብ ስንበላ ድካም ድካም እንቅልፍ እንቅልፍ የሚለን፡፡ በፆም ወቅት ግን ሰውነታችን ከዚህ ከባድ ስራ ላይ ስለማያተኩር በእግዚአብሄር ቃል ላይና በእግዚአብሄ ድምፅ ላይ ይበልጥ እንዲያተኩር ይረዳዋል፡፡
በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5፡8
· ሰው ከእግዚአብሄር አፍ በሚወጣ ቃል እንጂ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ይበልጥ ለማሳየት
ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።ዘዳግም 8:2-3
· ይበልጥ ራሳችንን ለመግዛት
ስጋችን የፈለግነውንም ለመስጠት በተጋን ቁጥር ይበልጥ ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን የሚፈልገውን ሁሉ ካልሰጠነው እየደከመ ይሄዳል፡፡ ስጋችን ሲደክምና ድምፁ እየቀነሰ ሲሄድ ስጋችንን ለመግዛትና በመንፈስ ለመትጋት ይመቸናል፡፡
ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡5
· በእግዚአብሄር ላይ ብቻ ለማተኮርና ድምፁን ለመስማት ይረዳናል እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። ሐዋርያት 13፡2
· ራሳችንን ለማዋረድና እግዚአብሄርን በብርቱ ለመፈለግ ያግዘናል እግዚአብሄር ትሁት እንዳያደርገን ከፈለግን ራሳችንን አስቀድመን ትሁት ማድረግ ማዋረድ እንችላለን፣፣መዝሙረ ዳዊት 35፡13
እኔስ እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስሁ፥ ነፍሴንም በጾም አደከምኋት ጸሎቴም ወደ ብብቴ ተመለሰ። 1ኛ ጴጥሮስ 5፡5-6
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakum…
Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on September 5, 2016, in Discipleship, From The Heart, Heart Matters, Wisdom. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: