ተነሺ፥ አብሪ

Free-woman-raising-arms-to-golden-sunset-summer-sky-like-praising.jpgብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ። እነሆ፥ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤ አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ። ኢሳይያስ 60:1-3

እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡፡ ተነሺ፥ አብሪ

የማብሪያሽ የመታያሽ የመድመቅሽ ዘመን ነው፡፡ ጊዜው የአንቺ ነው፡፡ ያንቺ ተራ ነው፡፡ ዘመንሽ ነው ይላል እግዚአብሄር፡፡

ለምን ይላል እግዚአብሄር ?

ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ይላል እግዚአብሄር፡፡ ክብርሽና በጎነትሽ መጥቶዋል፡፡ ተስፋሽ ደርሶዋል፡፡ ክፍያሽ መጥቷል፡፡ መድመቅሽ መጥቷል፡፡ የእግዚአብሄር መወደድ ፣ የእግዚአብሄር ሞገስ ፣ የእግዚአብሄር ውበት ፣ የእግዚአብሄር መፈለግ፣ የእግዚአብሄር መወደድ የእግዚአብሄር ነገር ባንቺ ላይ ነው፡፡

ስለ አካባቢሽ ደግሞ አታስቢ ይላል እግዚአብሄር ፡፡ ስለ አህዛብ ፣ ስለ አለም ሁኔታ ፣ ስለ አለም ኢኮኖሚ ፣ ስለ አለም አለመረጋጋትና ስለ አለም ጨለማ አታስቢ ይላል እግዚአብሄር፡፡ በአለም ላይ ያለው ሁኔታ ያንቺን ነገር አይነካውም ይላል እግዚአብሄር፡፡ በአለም ላይ ያለው የከፋ ጨለማ አንቺን ምንም አያደርግሽም ይላል እግዚአብሄር፡፡ የአለም አለማስተማመን በፍፁም አትመልከቺ ካንቺ መውጣትና መብራት ጋር አያገናኘውም ይላል እግዚአብሄር፡፡

እንዲያውም ይላል እግዚአብሄር የአለም ጨለማ ያንቺን ክብር ያበዛዋል ይላል እግዚአብሄር፡፡ የጨለማው ድቅድቅነት ያንቺን ብርሃን ክብር ያበዛዋል፡፡

አንቺን ከሌላው የሚይሽ እግዚአብሄር ነው፡፡ ሌሎቹ ላይ ጨለማ ሲወጣ አንቺ ላይ የእግዚአብሄር ብርሃን ፣ በጎነትና ክብር ይወጣል፡፡ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል ይላል እግዚአብሄር፡፡ እግዚአብሄር ባንቺ ይገለጣል፡፡ እግዚአብሄር ባንቺ ላይ ክብሩን ያንፀባርቃል፡፡ በጎነቱንና ክብሩን ለማሳየት እግዚአብሄር አንቺን  የሚጠቀምበት ጊዜው አሁን ነው፡፡

ይህ የእግዚአብሄር ክብር የማይስበው ሃያል የማይስበው ብረቱ የማይስበው በጎ ነገር የለም ይላል እግዚአብሄር፡፡

ካንቺ የሚጠበቀው ጊዜው አሁን እንደሆነ አውቀሽ ተነሺ አብሪ!

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#እግዚአብሔር #ክብር #በጎነት #አብሪ #ተነሺ #ጊዜውአሁንነው #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on August 26, 2016, in From The Heart, grace, Heart Matters. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: