ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን

Speak-to-your-mountain-537x357.jpgኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ። እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡22-23

እምነት የእግዚአብሄርን ሃይል የምንለቅበት መንገድ ነው፡፡ እምነት የእግዚአብሄር ሃይል በእኛ ቦታ እንዲሰራ የምናደርግበት መንገድ ነው፡፡ እምነት የእግዚአብሄር ሃይል በእኛ ምትክ እንዲንቀሳቀስ የማድረጊያው መንገድ ነው፡፡

በእምነት ውስጥ ተዝቆ የማያልቅ ሃብት አለ፡፡ በእምነት ውስጥ አስደናቂ እድል አለ፡፡ በእምነት ውስጥ አስበን ከምናውቀው በላይ የታመቀ ሃብት አለ፡፡

ኢየሱስም፦ . . .  ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ማርቆስ 9፡23

እምነትም የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ስንሰማ እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ነገር እናውቃለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ሰንሰማ እግዚአብሄር ያዘጋጀልንን አቅርቦት እንረዳለን፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል ስንሰማ እግዚአብሄርን እናምናለን፡፡ እምነት በእግዚአብሄ ቃል ይመጣል፡፡

እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17

ሰው ከእግዚአብሄር ቃል የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከተረዳ ያመነውን ነገር መናገር አለበት፡፡ ሰው ያመነበት ነገር እንዲሆን ባመነበት ነገር ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡ የሰው ንግግሩ ካመነው ነገር ጋር መስማማት አለበት፡፡ ሰው እንደ እምነቱ ሲናገር ያመነው ነገር ይፈፀማል፡፡ ያመነውን ነገር የሚሆነው የሰው ንግግሩ ከእምነቱ ጋር ሲስማማ ብቻ ነው፡፡ ሰው ያመነውን ሲናገረው ነው ያመነው ነገር የሚሆነው፡፡

እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡22-23

የሰው የእምነት ንግግር ወደመሆን ያመጣዋል፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች

የሚያስፈልገው አንድ ነገር

እምነት ይመጣል

የማይታይ እጅ

#እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

 

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on August 5, 2016, in Faith, From The Heart, Heart Matters. Bookmark the permalink. 1 Comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: