ስማችሁ በሰማያት ስለ ተጻፈ

book of lifec 22.jpgነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ። ሉቃስ 10፡20

እግዚአብሄር ለሃጢያታችን መድሃኒት ባዘጋጀው በእየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና ጌትነት በማመናችን ስማችን በህይወት መዝገብ ላይ ተፅፎአል፡፡ ስማችን በህይወት መዝገብ ላይ ስለተፃፈ ስንሞት ወይም ነፍሳችን ከስጋችን ሲለይ ከእግዚአብሄር ጋር ለዘላለም እንኖራለን፡፡

ነገር ግን እግዚአብሄር ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ እየሱስን የጣሉና  ያልተቀበሉ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀው ወደ እሳት ባህር ይጣላሉ፡፡ ምክኒያቱም በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ ሁሉ ለአሳቹ ለአውሬው ይሰግዳሉ፡፡

ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል። ራእይ 13፡8

በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ። ራእይ 20፡15

በምድር ላይ ከምናደርገው ማንኛውም ግኝትና ስኬት በላይ የሚያስደስተው ስማችን በህይወት መዝገብ ላይ ማፃፉና ወደመንግስተ ሰማያት እንደምንገባ ማረጋገጣችን ነው፡፡

በምድር ላይ ካሉ ደስታዎች ሁሉ ይልቅ ዘላቂው ደስታ ከእግዚአብሄር ጋር ለዘላለም እንድንኖር እግዚአብሄር እኛን ልጅ አድርጎ መቀበሉ ነው፡፡

በምድር ላይ ከምናገኛቸው ደስታዎች ሁሉ የሚበልጠው ከዚህ ጊዜያዊ ስጋ ስንለይ ዘላለማችንን የምናሳልፈው ከእግዚአብሄ ጋር መሆኑን ማወቃችን ነው፡፡

ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ። ሉቃስ 10፡20

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#መንግስተሰማያት #ዘላለም #ስም #የህይወትመዝገብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

 

 

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on August 4, 2016, in Faith, Uncategorized, Wisdom. Bookmark the permalink. 2 Comments.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: