ፀጋን በከንቱ

 

grace አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡1፣3-4
 
የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን ይላል ሃዋሪያው ፡፡ ሃዋሪያው እንደዚህ የሚለምነው ግን የእግዚአብሄርን ፀጋ በከንቱ መቀበል ምን ማለት ነው?
ሲጀመር ፀጋ ምንድ ነው? የእግዚአብሄርን ፀጋ በከንቱ መቀበል ማለትስ ምንድነው?
 
የእግዚአብሄር ፀጋ የእግዚአብሄር ችሎታ ወይም ሃይል ሲሆን እግዚአብሄርን መስለን በምድር ላይ እንድኖርና በምድር ላይ የተፈጠርንለትን አላማ እንድንፈፅም የሚያስችል ሃይል ነው፡፡
 
• የእግዚአብሄርን ፀጋ በከንቱ መቀበል ማለት ደግሞ ይህን ምንም ነገር የሚያስችለውን የእግዚአብሄር መለኮታዊ ሃይል ተቀብለን እንዳልተቀበልን በስንፍና በድካምና በሽንፈት መኖር ማለት ነው፡፡
 
• የእግዚአብሄርን ፀጋ በከንቱ መቀበል ወይም ማባከን ማለት “በሚያስችለኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።” (ፊልጵስዩስ 4:13) ያለውን ተመሳሳይ ፀጋ ተቀብለን እንዳልተቀበለ ፡ ምንም ሃይል እንደሌለውና የእግዚአብሄር እርዳታ ከእርሱ ጋር እንዳልሆነ ሰው በሽንፈት መኖር ማለት ነው፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስ የሚያግዘኝና የሚረዳኝ ፀጋው ነው በእኔ ሃይልና ብርታት አይደለም ይላል፡፡
 
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡10
 
• የእግዚአብሄርን ፀጋ በከንቱ መቀበል ማለት ወይም የእግዚአብሄርን ፀጋ በብላሽ መቀበል ማለት ማለት የራስን ድካም ብቻ ማየትና “ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና” (2ቆሮንቶስ 12.9) ያለውን ቃል አለመረዳትና የጌታን ስራ ለመስራት በትጋት አለመነሳት ነው፡፡
• የእግዚአብሄርን ፀጋ በከንቱ መቀበል ማለት ሁሉን የሚያስችለውን የፀጋው ክብር (ኤፌሶን 1፡6) ተቀብሎ ግን በዙሪያው ያሉትን ሁኔታዎች ማጋነን የተቀበለውን ፀጋ ግን በማሳነስ ወደፊት ለመቀጠል ሃሞት ማጣት ነው፡፡
 
• የእግዚአብሄርን ፀጋ በከንቱ መቀበል ወይም ማባከን የእግዚአብሄርን እርዳታ አለማየትና እግዚአብሄር ያስችላል ባለማለት ለህይወት ውጣ ውረዶች እጅ መስጠት ከህይወት መንገድ መመለስ ነው፡፡
 
• የእግዚአብሄርን ፀጋ በከንቱ መቀበል ማለት ነገሮች ሲጠነክሩና ችግር ሲመጣ በስፍራ አለመቆም “ይህ ሰው የሚያገለግለው በምቾት ብቻ ነው” ብለው ሰዎች እንዲሰናከሉ ማድረግ ነው፡፡
 
• የእግዚአብሄርን ፀጋ በከንቱ አለመቀበል ማለት ደግሞ የፀጋውን ባለጠግነት ተረድቶ በአስቸጋሪ ነገሮች ውስጥ ሁሉ ራስን አማጥኖ አገለግሎትን መፈፀም ነው፡፡
 
• የእግዚአብሄርን ፀጋ በከንቱ አለመቀበል ማለት “አልጋ በአልጋ ሲሆን ብቻ ነው የሚያገለግለው” እንዲሉ ለሰዎች ማሰናከያ አለመስጠት አስቀድሞ ኪሳራን በመተመን አገልግሎትን ላለመፈፀም ለምንም ሁኔታ እድል አለመስጠት ነው፡፡
 
ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡4-8
 
አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን . . ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡1፣4
 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

 

 

 

 

 

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on June 16, 2016, in Faith, From The Heart, Heart Matters, Leadership, Uncategorized, Wisdom. Bookmark the permalink. 1 Comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: