እርሱን እወቅ 

እንዲከናወንለትና እንዲሳካለት የማይፈልግ ሰው በምድር ላይ አይገኝም ፡፡ ሁሉም ሰው የክንውንንና የስኬት መንገድ በብርቱ ያስባል፡፡ ምክኒያቱም እኛ ስንፈጠር ታቅደን የተሰራነው እንዲሳካልንና እንዲከናወንልን ነው፡፡ ስለዚህ ነው  ክንውንና ስኬት ደስ የሚለን የሚያረካን፡፡

ወደ እውነቱ ስንመጣ ግን ሰው ሁሉ አይሳካለትም ፡፡ የሚሳካለት ሰው አለ፡፡ የማይሳካለት ሰው አለ፡፡  ስለ ስኬት የሰራን እግዚአብሄር ምን ይላል የሚለውን ጥያቄ በትክክል መመለስ የምንችለው ከቃሉ ከመፅሃፍ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡

በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። ምሳሌ 3፡6

ለእግዚአብሄር ክብር የተፈጠርነው እኛ እንዲሳካልን በአካሄዳችን ሁሉ ለእርሱ እውቅና መስጠት ይጠበቅብናል፡፡ ግን እርሱን ማወቅ ማለት ምንድነው?

  • እርሱን ማወቅ ማለት እግዚአብሄር የህይወታችን ባለቤትነት መሆኑን መቀበል ማለት ነው፡፡
  • ለእርሱ እውቅና መስጠት ማለት ለእኛ እግዚአብሄር ከእኛ በላይ እንደሚያውቅልንና እንደሚያስብልን መቀበል ማለት ነው፡፡
  • እርሱን ማወቅ ማለት እርሱ የህይወታችን ጌታ መሆኑንንና እኛ የሱን ፈቃድ ለመፈፀም ያለን የእርሱ አገልጋዮች መሆናችንን መረዳት ነው፡፡
  • እርሱን ማወቅ ማለት “ያንተ ፈቃድ ይሁን የኔ ፈቃድ አይሁን” በማለት እርሱ ለህይወታችን ያለውን ምርጫ መከተልና ሁል ጊዜ እርሱን ለማስደሰት መቅናት ነው፡፡
  • ለእርሱ እውቅና መስጠት ማለት የምናደርገው ነገር እግዚአብሄርን ያስደስተዋል ወይስ ያስከፋዋል ብለን በቅንነት በመጠየቅ የሚያስደስተውን ማድረግ የማያስደስተውን መተው ነው፡፡
  • ለእርሱ እውቅና መስጠት ማለት እርሱ የሚወደውን በመውደድ እርሱ የማይወደውን በመጥላት ከእርሱ ጋር መተባበር ነው፡፡
  • ለእርሱ እውቅና መስጠት “እኔ በራሴ ላይ ጌታ አይደለሁም በኔ ላይ ጌታ እየሱስ ነው” ብሎ ለእየሱስ ጌትነት ቦታ መስጠትና በህይወታችን ውሳኔ ከመወሰናችን በፊት የእርሱን ሃሳብ መስማትና እንደ ፈቃዱ ውሳኔያችንን ማስተካከል ነው፡፡
  • ለእርሱ እውቅና መስጠት ማለት የእግዚአብሄርን ፈቃድ ከስሜቴና ከደስታዬ በላይ አከብራለሁ ማለት ነው፡፡

እግዚአብሄርን እንደ አምላክነቱ እውቅና ከሰጠኸው እርሱ ጎዳናህን ያቀናልሃል፡፡ እግዚአብሄር ጎዳናህን ካቀና እንዳይሳካልህ ሊያደርግ የሚችል ምንም ሃይል አይኖርም፡፡

እውቅና ባልሰጠኸው ነገር ውስጥ ገብቶ ግን ያንተን ጎዳና ለማቃናቱ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ለእግዚአብሄር እውቅና ላለመስጠት በሰሰትክበት ነገርህ ውስጥ እግዚአብሄር ጎዳናዬን ያቃናልኛል ብለህ መጠበቅ ድፍረቱም የለህም፡፡ በሁሉ እንዲሳካልህ ከፈለግህ በመንገድህ ሁሉ እውቅና ስጠው፡፡

በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። ምሳሌ 3፡6

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakum…

 

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on June 16, 2016, in Uncategorized. Bookmark the permalink. 2 Comments.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: