ጥበበኛ የኢንቨስትመንት

welcomeበአለም ላይ ለመዋዕለ ኑዋይ ማፍሰስ ወይም ኢንቨስትመንት ጥሩ ምላሽ የሚያስገኙ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ለማግኘት ወይም ለማጥናትና ለመፍጠር ሰዎች ሌት ተቀን ጥረት ያደርጋሉ፡፡

በተለይ መጠነ ሰፊ የቤት ግንባታ ወይም ሪልስቴት ወይም የፋይናንስ ኢንቨስትመንትና የገንዘብ አገልግሎት ዘርፎችች ብዙ ምላሽ ከሚሰጡት የኢንቨስትመንት እድሎች ከሚጠቀሱት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ችግሩ ግን ገንዘብን ካከማቸን በሁዋላ ይህንን ገንዘብ ይዘን ወዴትም መሄድ አለመቻላችን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እዮብ

ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ ኢዮብ 1፡21 እንዳለው በዚህ ምድር ያከማቸነውን ገንዘብን የትም ይዘነው መሄድ አንችልም፡፡

አንድ የመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪ ነበሩኝ፡፡ ወደሰማይ አንድ ነገር ይዤ እንድሄድ ቢፈቀድልኝ መፅሃፍ ቅዱሴን ነበር ይዤ የምሄደው ይሉ ነበር፡፡ ነገር ግን መፅሃፍ ቅዱስንም ሆነ ማንኛውም ገንዘብን የመሬት ስበት ይዞ ስለሚያስቀረው ወደሰማይ ይዞ መሄድ አይቻልም፡፡

የምስራቹ ግን አንድ ነገር ይዘን ለመሄድ መቻላችን ነው፡፡

በዚህ የመሬት ስበት ይዞ በሚያስቀረው ጊዜያዊ ገንዘብ ተጠቅመን ሰዎችን ለክርስቶስ መማረክና ከእኛ ጋር ወደ መግስተ ሰማያት የሚሄዱ ወዳጆችን ማፍራት እንችላለን፡፡

እየሱስ እንዲህ አለ፡፡

እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16፡1-9

በዚህ ጊዜያዊ ገንዘብ ተጠቅመን ሰዎች ስለጌታ እየሱስ አዳኝነት እንዲሰሙ ማድረግ እንችላለን፡፡ በምድር ገንዘብ ሰዎች ጌታን እስከፍፃሜው እንዲከተሉ ልናገለግላቸው እንችላለን፡፡

ጊዜያዊውን ገንዘባችንን ጉልበታችንንና ጊዜያችንን ተጠቅመን በዘላለም ቤቶች የሚቀበሉንን ዌልካም የሚሉን ሰዎችን ማገልገል እንችላለን፡፡ ገንዘባችንን ተጠቅመን እየሱስ በመሰቀል ላይ ለሰው ልጆች የሰራውን የማዳን ስራ በማብሰር ብዙዎችን ወደ ዘላለም ህይወት እንዲገቡ መርዳትና ማገልገል እንችላለን፡፡

ይህ ነው እንግዲህ ወደር የለሹ ዘላለማዊ ኢንቨስትመንት፡፡

https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

Seeking the kingdome fisrt is true prosperity

 

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on June 6, 2016, in Uncategorized. Bookmark the permalink. 2 Comments.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: