የፍርሃት ኢላማ

fear purposeእግዚአብሄር ለሰዎች የሰጣቸውን ሃላፊነት እንዳይወጡ ሰይጣን የሚገዳደርበት ዋነኛ መሳሪያው ፍርሃትና ማታለል ነው፡፡  የማናውቀውን እውነት ተጠቅሞ ሰይጣን ህይወታችንን ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ይመጣል፡፡

የእግዚአብሄር አላማ ብንረዳም እንኳን ሰይጣን የተሸነፈ ጠላት ስለሆነና በሌላ በምንም ሊያስቆመን እንደማይችል ስለሚያውቅ በፍርሃት ሊያስቆመን ይሞክራል፡፡

ለዚህ ነው እየሱስ ብዙ ጊዜ አትፍራ እያለ የሚያበረታታው፡፡

ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ። እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው። ማርቆስ 5፡36

ሰይጣን በህይወታችን ፍርሃትን ሲልክ በአላማ ነው፡፡ ሰይጣን ፍርሃትን የሚልከው እንደው የፍርሃት ስሜት እንዲሰማን ብቻ ሳይሆን በፍርሃት ሃሳባችንን እንድንለውጥ ከጉዞዋችን ሊያደክመንና በፍርሃት ሊያሽመደምደን ነው፡፡

የሚሰማንን የፍርሃት ስሜት ከተቀበልንና በፍርሃት ስሜታችን ከተመራን ከእርምጃችን እንስተጉዋጉላለን፣፡፡ ወደፊት መሄድ ያቅተናል፡፡ ወደፊት ካልሄድንና እግዚአብሄርን ቃል ካልታዘዝን የእግዚአብሄር ፈቃድ በህይወታችን አይከናወንም፡፡

የእግዚአብሄርን ሃሳብ አደረግን ማለት የፍርሃት ስሜት አይሰማንም ማለት በፍፁም አይደለም፡፡ ወይም የእግዚአብሄር ፈቃድ ማድረጋችን ምልክቱ የፍርሃት ስሜቱ ፈፅሞ አለመሰማት አይደለም፡፡

እንዲያውም ድፍረት ወይም መተማመን የፍርሃት ስሜት እጥረት ወይም አለመኖር ሳይሆን በፍርሃት ስሜት አለመሸነፍ ነው፡፡

ስለዚህ ነው የእግዚአብሄርን ፈቃድ የፍርሃት ስሜቱ እያለ አድርገው የሚባለው፡፡ ወይም የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ የፍርሃት ስሜቱ እስከሚጠፋ ከጠበቅክ መቼም እግዚአብሄርን ልትታዘዘው አትችልም የሚባለው፡፡

for more from Abiy Wakuma Dinsa

 

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on June 4, 2016, in Uncategorized. Bookmark the permalink. 1 Comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: