መተው ያበለፅጋል

releasingበክርስትና አጥብቀን የምንይዛቸው ብዙ ነገሮች በመኖራቸው መተው የሚለው ሃሳብ ብዙም የተለመደና ተወዳጅ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሚዛናዊ የክርስትና እርምጃ እንዲኖረን በእምነት አጥብቀን ከምንይዛቸው ነገሮች ባልተናነሰ ሁኔታ መተው የሚያስፈልገን ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህ መተው የሚገባንን ነገሮች ካልተውን ህይወታችን እግዚአብሄር እንዳቀደው መሻገር አይችልም፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ መተው የክርስትና ህይወታችን ቁልፍ እንደሆነና እንዲያውም ነፍሳችንን የምናገኛት በመተው መሆኑን እየሱስ ያስተምራል፡፡
ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል። ማርቆስ 8፡35 የእግዚአብሄር በረከት ከእነዚህ ሁሉ ያለፈ ስለሆነ የገንዘብና የንብረት ማታለልን እንድንተው መፅሃፍ ያስተምረናል፡፡
የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ። ዕብራውያን 10፡34-35
የእምነት አባቶችም ስለተመሰከረላቸው ኑሮ ሲናገር ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዕብራውያን 11፡37
ስለሙሴ እምነት ሲናገር ምቾትን እንዳስተወውና መከራን እንዳስመረጠው ይናገራል፡፡
ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ፤ ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና። የንጉሡን ቍጣ ሳይፈራ የግብፅን አገር የተወ በእምነት ነበር፤ ዕብራውያን 11፡24-27
እንዲሁም በደልን እንድንንተውና በሰዎች ላይ እንዳንይዝባቸው መፅሃፍ ያስረተምረናል፡፡ እንዲያው ይቅር ካላልን ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት ትክክል እንደማይሆን መፅሃፍ ያስተምራል፡፡
ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት። እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም። ማርቆስ 11፡25-26
በህይወታችንን የምንተዋቸው ነገሮች አሉ፡፡ የእኛ ብልግናና ስኬት ከሰዎች ጋር ስለማይያያዝና እኛን ችሎ ሊያሳጣንና ሊያደኸየን የሚችል ሰውም ሆነ ሁኔታ የለም፡፡ ስለዚህ ነገሮችን በተውን ጊዜ ሁሉ ይበልጥ እየተፈታን እየተለቀቅን እንዲሁም ይበልጥ እየበለፀግን እንጂ እየከሰርን አንሄድም፡፡
Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on June 3, 2016, in Uncategorized. Bookmark the permalink. 6 Comments.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: