እመን ብቻ እንጂ አትፍራ!

እመን ብቸበክርስትና ጉዞ እግዚአብሄር ወዳየልን የህይወት ስፍራ ለመግባትና የእግዚአብሄርን አላማ ፈፅመን እርሱን ለማክበር እንዳንችል የሚያስፈራሩ ከጉዞዋችን ሊያስቀሩን የሚመጡ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡

እነዚህን ብዙ ነገሮች መስማትና መከተል እንደሌለብን ፤ ይልቁንም ማድረግ ያለብንን እየሱስ እንዲህ በማለት ይገልፀዋል፡፡

እመን ብቻ እንጂ አትፍራ

በህይወታችን ጊዜያችንንና ጉልበታችንን ልንሰጠው የማይገባው ነገር ፍርሃት ነው፡፡ በልባችን ስፍራ ልንሰጠው የማይገባው ነገር ጭንቀትና ፍርሃት ነው፡፡

በህይወታችን ደግሞ ጊዜያችንን ልናሳልፍበትና በትጋት ልንገነባው የሚገባው ነገር እምነትን ነው፡፡በህይወታችን ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ነገር እምነት የሚመጣበትን የእግዚአብሄርን ቃል መስማት ነው፡፡ በህይወታችን ልንመካበት ደስ ልንሰኝበት ልንጓደድበት የሚገባው ነገር እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን ፈቃዱን ነው፡፡ በህይወታችን ልባችንን ልንጥልበት በሙሉ ልባችን ተስፋ ልናደርገው የሚገባው ነገር የእግዚአብሄርን ቃል ነው፡፡

ከእኛ የሚጠበቀው ነገር ሌሎቹን “ እኛን ስማን ተከተለን” ካለበለዚያ “ወዮልህ ጠፋህ ተበላህ” የሚሉትን ብዙ ድምፆች ትተን እግዚአብሄር ስለህይወታችን ያለውን አላማ በቃሉ በማግኘት ቃሉን መቀበልና በእምነት መኖር ብቻ ነው ፡፡

እመን ብቻ እንጂ አትፍራ፡፡ ማርቆስ 5፡36

እግዚአብሄር ለልጆቹ ለእኛ ያዘጋጀውን ከቃሉ ተረድተን እንደቃሉ በእምነት ከቀረብነው እግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ ለሁላችን የሚበቃ ሃብት አለው፡፡ የሃብትና የአቅርቦት ችግር የለበትም፡፡ እግዚአብሄር ግን እንደልጅ በእምነትና በድፍረት እንድንቀርበው ይፈልጋል፡፡

በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ሮሜ 10፡12

እመን ብቻ እንጂ አትፍራ፡፡

Advertisements

About AbiyWakumaDinsa

Johannesburg, South Africa

Posted on April 9, 2016, in Uncategorized. Bookmark the permalink. 6 Comments.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: